
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል የጀመርነውን የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአርባ ምንጭም ቀጥለናል ብለዋል፡፡
በዚህ መርሐ ግብር መትከል ብቻ ሳይሆን የተከልናቸውን በመከታተልና በመንከባከብ ዛፍ ሆነው ከሚሰጡት ውበት በተጨማሪ ፍሬ እንዲያፈሩ መሥራት ይጠበቅብናል ነው ያሉት፡፡
የአርባ ምንጭ ሕዝብ ላደረገልን የሞቀ አቀባበል እናመሠግናለን ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!