
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአርባ ምንጭ የተፈጥሮ ስጦታው ታላቅ ተስፋን የመጫሩን ያህል የአካባቢውን ምሉዕ አቅም ለመጠቀም የሠራነው ጥቂት በመሆኑ ደግሞ ያስቆጫል ሲሉ ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የ’ገበታ ለትውልድ’ ፕሮጀክት በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዚህ “የምድር ገነት” ድርሻ በመግዛት ኢንቨስት ለማድረግ እድል አቅርቧል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!