ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የሕዝብ ለሕዝብ እና የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሠሩ አስታወቁ።

79

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የጋራ ድንበር አሥተዳዳሪዎች ስብሰባ በስኬት ተጠናቅቋል። የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመራሮች የጋራ ድንበር አሥተዳደር ስብሰባ ማካሄዳቸውን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙኅን በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በዚህም የሁለቱን ሀገራት የሕዝብ ለሕዝብ እና የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሠሩ ተጠቁሟል።
ድንበር ተሻጋሪ ደህንነትን እና የጋራ ልማትን ለማጎልበትም መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማኀበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስነበበው በውይይቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ማንዴ ሴማይ ኩምባ፣ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኡመድ ኡጁሉ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር) እንዲሁም የደቡብ ሱዳን የክልል አሥተዳዳሪዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በዜጎች መካከል የቆዩ የአብሮነት፣ የመከባበር፣ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት እሴቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መሥራት ይገባል” የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት
Next articleየአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዓለም አቀፍ ዕውቅናን እንዳገኘ እና ለመጪው ትውልድ የሚጠቅም ትሩፋት እንዳለው አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡