
ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 29ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። በጉባኤው በቀረበው የሰላም እና ፀጥታ መምሪያ ሪፖርት ላይ ማብራሪያ የሰጡት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው በክልሉ ብሎም በብሔረስብ አሥተዳደሩ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ለዘመናት በዜጎች መካከል ያለውን የአብሮነት እና የአንድነት እሴት እንዳይሸረሽር ሁሉም መሥራት አለበት ብለዋል።
የዜጎችን የቀደመ የአብሮነት፣ የመከባበር፣ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት እሴቶች እንዲመለሱ ለቀጣይ መሥራት እንደሚገባም ዋና አሥተዳዳሪው አስገንዝበዋል። ለምክር ቤቱ የብሔረሰብ አሥተዳደሩን የሰላም እና የፀጥታ ሥራዎች ሪፖርት ያቀረቡት የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የሰላም እና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊ ጌታቸው ቢሻው የተፈጠረውን ግጭት ለመቀነስ እና የቆዩ የሰላም እሴቶችን ለመገንባት ሕዝባዊ ኮንፈረንሶች መካሄዳቸውን መናገራቸውን ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!