“ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች እንደሚሳተፉ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።

13

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን በዘንድሮው የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራ በአረንጓዴ አሻራ፣ በደም ልገሳ፣ በክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት፣ የአቅመ ደካሞችን ቤት በመጠገን እና በሌሎችም ተግባራት ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ቢሻው ሞላ “የበጎ ፈቃድ ሥራ ሰላምን የሚፈልግ ተግባር ቢኾንም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ኾኖ መልካም ተግባራትን ማከናወን ከወጣቶች የሚጠበቅ ኀላፊነት መኾኑን” ተናግረዋል፡፡

ኀላፊው በዞኑ ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶች በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች ይሳተፋሉ ነው ያሉት፡፡ አቅም ለሌላቸው ዜጎች ቤት የመጠገን እና አዲስ ቤት የመገንባት ሥራም እንደሚከናወን አስገንዝበዋል፡፡ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም ከ100 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትክል ስለመታቀዱም ነው የተገለጸው፡፡ በደም ልገሳ ተግባርም 1ሺህ 200 በላይ ዩኒት ደም ለመሠብሠብ በዕቅድ እንደተያዘ ኀላፊው አብራርተዋል፡፡ ወጣቶች ከምንም በላይ ለሰላም መረጋገጥ ኀላፊነታቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ኀላፊው የማኅበረሰቡን ችግር መፍታት የሚቻለው የበጎነትን እሴቶች በማጎልበት በመኾኑ የበጎ ፈቃድ ሥራው ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ሀገራዊ ኀለፊነትን መወጣት ይገባል ብለዋል፡፡ የወጣቶች የበጎ ፈቃድ ሥራ በዞኑ ይወጣ የነበረን ከ690 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ማስቀረት የሚያስችል ስለመኾኑም ተገልጿል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመምህራን የሰጡት እውቅና ትውልድን የመቅረጽ ተግባራችንን አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያነሳሳ ነው” የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር
Next articleለ2016 ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውን የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ተፈታኝ ተማሪዎች ተናገሩ።