“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመምህራን የሰጡት እውቅና ትውልድን የመቅረጽ ተግባራችንን አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያነሳሳ ነው” የኢትዮጵያ መምህራን ማኀበር

35

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሰጡት ማብራሪያ እና ምላሽ ኢትዮጵያን ከሚያስቀጥሉ ምሰሶዎች መካከል አርሶ አደር፣ ወታደር እና መምህራን ወሳኝ ስለመኾናቸው አንስተዋል።

አርሶ አደሩ እያመረተ በኑሮ ሁኔታ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እያመጣ መኾኑን ጠቅሰው፤ መምህራን እና ወታደሮች ደግሞ ለኢትዮጵያ ቀጣይነት ዋጋ የሚከፍሉ፣ እውቀታቸውን እና ሕይወታቸውን ሳይሰስቱ የሚሰጡ መኾናቸውን ጠቁመዋል፡፡ ይህንን የተከታተሉት የኢትዮጵያ መምህርን ማኀበር ፕሬዝዳንት ዩሐንስ በንቲ (ዶ.ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለመምህራን የሰጡት እውቅና ትውልድን የመቅረጽ ተግባራችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ተነሳሽነት የሚፈጥር ነው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገሪቱ የመጨረሻው ሕግ አውጪ አካል በኾነው ምክር ቤት ፊት የሰጡት እውቅና ሕብረተሰቡ ለመምህራን ዘወትር ክብር መስጠት እንዳለበት የሚያስገነዝብ መኾኑንም ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ መምህራን ሁሌም ሀገር እና ትውልድን አስቀድመው እንደሚሠሩ ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለዘመናት ባለፈችባቸው የትውልድ ግንባታ ሂደት ውስጥም ትልቁን ሚና እንደሚይዙ ጠቁመዋል፡፡

እንደ ኢዜአ ዘገባ የኢትዮጵያ መምህርን ማኀበር ፕሬዝዳንት ዩሐንስ በንቲ (ዶ.ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ መምህራን ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች አቅም በፈቀደ አግባብ መንግሥት ለመመለስ እንደሚሠራ መግለጻቸውም የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለምን አንጠቀምም” አርሶ አደሮች
Next article“ከ600 ሺህ በላይ ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ሥራዎች እንደሚሳተፉ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ወጣቶች እና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።