የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች በምክክር ሂደቱ እያበረክቱ ያለውን በጎ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሳሰበ።

17

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ለመገናኛ ብዙኅን ባለሙያዎች ያዘጋጀው የሥልጠና እና የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ማሕሙድ ድሪር የመገናኛ ብዙኀን ባለሙያዎች የኮሚሽኑን ዓላማ ለማሳካት በጎ ሚና እየተጫወቱ መኾኑን ጠቅሰው ለዚህ ሚናቸው በኮሚሽኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል። በቀጣይ በሚከናወኑ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶች ላይም የጀመሩትን በጎ ሚና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ነው ኮሚሽነሩ ጥሪ ያቀረቡት።

የሥልጠና እና የውይይት መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ሲኾን ጋዜጠኞች ከኮሚሽኑ ከፍተኛ ባለሙያዎች ጋር ተገናኝተው በአጠቃላይ የምክክሩ ሂደት ላይ እየተወያዩ ነው፡፡ ጋዜጠኞች በሀገራዊ ምክክሩ ዙሪያ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ ለቀጣይ ሥራቸው ግብዓት መስጠት የስልጠና እና የውይይት መድረኩ ዓላማ ነው፡፡

በመድረኩ የመገናኛ ብዙኀን ተቋማት በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ያላቸውን ሚና በተመለከተ የሌሎች ሀገራት ተሞክሮ ቀርቦ ልምድ የሚወሰድበትም መኾኑን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያሰፈረው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ36 ሺህ በላይ ወጣቶች ይሳተፋሉ” የደብረታቦር ከተማ አሥተዳደር
Next articleለ900 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩን የአማራ ክልል ሥራ እና ሥልጠና ቢሮ ገለጸ።