“በኢትዮዽያ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ 10 ሺህ 467 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

25

ባሕር ዳር: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ካሉበት ውስብስብ ችግሮች ወጥቶ ለውጥ ላይ እንደኾነ ጠቁመዋል።

የሕዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ሥራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ተሠርቷል ብለዋል። የተከናወኑት ተቋማዊ ለውጦችም በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎችን እንዳመጡም ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአብነት ያነሷቸው ለውጦችም ለምሳሌ ያክል፦
👉 በቀን 900 ፓስፖርት መስጠት የነበረውን አገልግሎት ወደ 1 ሺህ 700 ማድረስ ተችሏል።
👉 ቀደም ብለው የተጠራቀሙ ጥያቄዎችን አስተናግዶ ለመጨረስ በተሠራ ሥራ 1 ሚሊዬን ፓስፓርት ታትሞ ገብቶ እስከ 87 በመቶ ተሰራጭቷል።
👉 የተከማቹ ቅሬታዎች መቶ በመቶ ተፈትተዋል።
👉 በኢትዮዽያ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ 10 ሺህ 467 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል።
👉 ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ 18 ሺህ ሰዎች ቅጣት እንዲከፍሉ ተደርጓል።
👉 በ88 ሀገሮች የቪዛ አገልግሎት በመክፈት ለ81 ሺህ 927 ተስተናጋጆች ኢ-ቪዛ ጨምሮ የቪዛ አገልግሎት ተሰጥቷል።
👉 ለ4 ሚሊየን 276 ሺህ 474 ግለሰቦች በአየርና በየብስ መዳረሻ ጣቢያዎች አገልግሎት ተሰጥቷል

በአሁኑ ወቅትም ተቋሙን የዘመነ እና አገልግሎቱን በጥራት የሚሰጥ ተቋም ለማድረግ ብዙ ሥራዎች እየተሰሩ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየደብረ ብርሃን የኮሪደር ልማት በአረንጓዴ አሻራ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ከተማ አሥተዳደሩ አስታወቀ።
Next articleየተፈጥሮ ማዳበሪያ በማዘጋጀት እና በመጠቀም ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚገባ ግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡