የደብረ ብርሃን የኮሪደር ልማት በአረንጓዴ አሻራ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ከተማ አሥተዳደሩ አስታወቀ።

20

ደብረ ብርሃን: ሰኔ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር የ2ኛው ምዕራፍ 2ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መረሐ ግብር እና የክረምት ሥራዎች የንቅናቄ መድረክ “የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ይገኛል። የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት ዓለምን ስጋት ላይ እየጣላት እና ህልውናችንን እየተገዳደረ የሚገኘውን የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ሚናው የጎላ መኾኑን ተናግረዋል።

በክረምት ወራት ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ ሁሉም የበኩሉን በማድረግ ከመትከል ባለፈ እንክብካቤው ላይ በትኩረት መሥራት ይጠበቃል ብለዋል። በተለይ ከተረጅነት እና ከልመና ለመላቀቅ የግብርናው ዘርፍ ሚናው የጎላ በመኾኑ የሁሉም ርብርብ ያስፈልገዋል ብለዋል። በተለይ የደብረ ብርሃን የኮሪደር ልማት በአረንጓዴ አሻራ ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው በንግግራቸው ገልጸዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ግብርና መምሪያ ኅላፊ መርሻ አይሳነው በበኩላቸው በዘንድሮ አመት ከ7 ነጥብ 1 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በ625 ሄክታር መሬት ላይ ይተከላሉ ብለዋል። ለዚህም የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል። በንቅናቄ መድረኩ ከከተማ አሥተዳደሩ እና ከቀበሌ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

ዘጋቢ፦ ፋንታነሽ መሃመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኑሮ ውድነትን እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን መፍታት በቀጣይ ትኩረት እንደ ሚሰጠው የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት ገለጸ፡፡
Next article“በኢትዮዽያ በሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ 10 ሺህ 467 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)