
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በቦሩ ሜዳ የተገነባው ትምህርት ቤት ከዓለም ባንክ በተገኘ 25 ሚሊየን ብር ድጋፍ ነው።
10 ክፍሎች ያለው ሦስት ብሎክ እና ሁለት ዘመናዊ የመጸዳጃ ቤቶችን የያዘ ነው። የመማሪያ ክፍሎቹም ከ300 በላይ ጠረንጴዛ እና ወንበር ተሟልቶላቸዋል። የደሴ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኅላፊ ፍቅር አበበ በከተማ አሥተዳደሩ በርካታ ልማቶች ተገንብተው ተመርቀዋል ብለዋል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ የቦሩሜዳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መኾኑን ገልጸዋል።
በቀጣይ ዓመት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመገንባት መታቀዱን ገልጸዋል። ከትምህርት ቤቱ በተጨማሪም የመሠብሰቢያ አዳራሽ ግንባታን እና የውኃ ቅርቦት ችግር ይፈታል ብለዋል። ከተማ አሥተዳደሩም የገጠሩን ማኅበረሰብ በልማት ለማዳረስ እየሠራ ነው ያሉት መምሪያ ኅላፊው የተገነቡ ትምህርት ቤቶችን ማኅበረሰቡ እንዲጠብቅ ጠሳስበዋል።
“ወላጆችም ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሠጥ የናንተ ድርሻ ትልቅ ስለኾነ ልጆችን በማብቃት ልታግዙ ይገባል” ማለታቸውን የደሴ ከተማ አሥተዳደር ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!