ባለፋት 11 ወራት 466 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ገለጹ።

29

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሠባ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ገቢ እና ወጭን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እንዳሉት በበጀት ዓመቱ መንግሥት 529 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ባለፉት 11 ወራት 466 ቢሊዮን ብር ሰብስቧል። የዕቅዱን 96 በመቶ አሳሳክቷል ነው ያሉት።

👉 ወጭን በተመለከተ 730 ቢሊዮን ለማውጣት አቅዶ 716 ቢሊዮን ብር ወጭ ኾኗል። ይህም 98 በመቶ መኾኑ ነው።
👉 በገቢ እና ወጭ መካከል ያለው የበጀት ጉድለት 2 ነጥብ 5 ነው።
👉 በወጭ እና ገቢ ውስጥ ኮንትሮባንድ፣ የገቢ ሥወራ እና የንግድ ማጭበርበር ገቢ ለመሰብሰብ ጋሬጣ ኾኗል።
👉 ከጂዲፒ ግብር የሚሰበሰበው 7 በመቶ ብቻ ነው።
👉 ከለውጡ በፊት በሁሉም መስኮች 19 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ይገኝ ነበር። ከለውጡ በኋላ 23 ቢሊዮን ዶላር ማመንጨት ተችሏል።
👉 ዘንድሮ ወደ ውጭ ከወጣው ሸቀጣሸቀጥ 10 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
👉 ጥራጥሬ፣ ቡና፣ አበባ፣ ወርቅ… አምና ከነበረው ገቢ ዘንድሮ መሻሻል አሳይተዋል። ዘንድሮ ወደ ውጭ ከተላከው ከአምናው በአራት በመቶ አድጓል።
👉 ሪሚንታንስ ከአምናው ከ6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
👉 ወደ ሀገር ውስጥ ከምናስገባው ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሀገር ውስጥ ተመርቶ መሸፈን ተችሏል።
👉 40 በመቶ የፋብሪካ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት ተችሏል።
👉 ለነዳጅ በየዓመቱ ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ይወጣል። ለማዳበሪያ 1 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ወጭ ይኾናል። ለዕዳ ክፍያ 2 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ይኾናል።
👉 በአጠቃላይ በበጀት ዓመቱ ለነዳጅ፣ ለአፈር ማዳበሪያ እና ለዕዳ ክፍያ 7 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ኾኗል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምርት እና ምርታማነት እያደገ ሲሄድ የኑሮ ውድነቱም እየተሻሻለ ይሄዳል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው፡፡