
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ)6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሠባ እየተካሄደ ነው፡፡
በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሠባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ተገኝተዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ሊመልሷቸው ይገባል ያሏቸውን ጥያቄዎችም አንስተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በሀገሪቱ የታጠቁ ኀይሎችን ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተሠሩ ሥራዎች እና የተገኙ ውጤቶች እንዲብራሩላቸው አንስተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት የትምህርት ግብዓት ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት እየሠራው ያለውን ሥራ በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲያብራሩም ጠይቀዋል፡፡
በክልሎች ያለውን የግብር አሠባሠብ ችግር ለማስተካከል እየተሠራ ያለው ሥራ እንዲብራራ የጠየቁት የምክር ቤቱ አባላት የታክስ ሥርዓቱን ፍትሐዊነት ለማረጋገጥ ምን እንደታሰበ ማብራሪያ ጠይቀዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!