በደሴ ከተማ አሥተዳደር የ2016 ዓ.ም የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።

13

ደሴ: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዛሬው የማስጀመሪያ መርሐ ግብር የአቅመ ደካሞች ቤት ጥገና፣ የደም ልገሳ፣ የችግኝ ተከላ እና የፅዳት ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የተወጣጡ ድንበር ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ጨምሮ ከ83 ሺህ በላይ የሚኾኑ ዜጎች በ14 ዘርፎች ተሳታፊ እንደሚኾኑ ተገልጿል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከ94 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪን እንደሚያስቀር እና ከ140 ሺህ በላይ የሚኾኑ ወገኖችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ዘጋቢ:- አንተነህ ፀጋዬ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለ5ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።
Next articleየታጠቁ ኀይሎችን ወደ ሰላማዊ መንገድ ለመመለስ እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የተሠሩ ሥራዎች እና የተገኙ ውጤቶች እንዲብራሩላቸው የምክር ቤት አባላት ጠየቁ፡፡