የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ጥያቄዎች፡-

21

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

👉 ስለ ሀገራዊ ምክክር እና ሽግግር ፍትሕ ተደጋግሞ ይነሳል፤ መንግሥት በሕዝብ ዘንድ እምነት ለመገንባት ምን እየሠራ ነው?
👉 የመስኖ ፕሮጀክት፣ የመንገድ እና የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ ባለመጠናቀቃቸው በማኅበረሰቡ ዘንድ ቅሬታ እየተነሳና ነው፤ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እንደ መንግሥት ምን ታስቧል?
👉 መንግሥት ሰላማዊ የፖለቲካ ባሕልን ለማደበር ጥረት እያደረገ ነው፤ የቆዩ ችግሮችን ለመፍታት እየሠራ ነው። የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ጥሩ ነው፤ ነገር ግን ነፍጥ አንግበው የሚንቀሳቀሱ አካላት በሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳተፉ ለማድረግ ምን እየተሠራ ነው?
👉 በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ስኬታማ የዲፖሎማሲ ሥራ ተሠርቷል፤ በተጨባጭ አሁን ላይ የውጭ ግንኙነታችን ምን ደረጃ ላይ ነው? ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለን ግንኙነት ተጨባጭ ሁኔታ ማብራሪያ ቢሰጠን??

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡
Next articleእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለ5ኛ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ።