6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት እየተካሄደ ነው፡፡

36

ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ሥብሰባ በ2016 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት የሥራ አፈጻጸም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ነው፡፡

የምክር ቤት አባላት ያነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች፡-

👉 በአዲስ አበባ የተጀመረው ልማት በሌሎች አካባቢዎች ለማስቀጠል የተያዘ አቅጣጫ አለ ወይ?
👉 በፕሪቶሪያል ስምምነት ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት እና የዜጎችን ደኅንነት ለማስጠበቅ መንግሥት ቁርጠኝነት አሳይቷል፡፡ ነገር ግን በፕሪቶሪያው ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ የሚነሱ ውዥምብሮች በሕዝብ ዘንድ ጥርጣሬ እየፈጠረ ነው፤ አፈጻጸሙ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
👉 ከስምምነቱ በኋላ በአማራ፣ በትግራይ እና በአፋር ክልሎች የመልሶ መቋቋም ሥራዎች ምን ይመስላሉ?
👉 የአዋሽ- ኮምቦልቻ -ሃራ ገበያ የባቡር ፕሮጄክት ሥራ መልሶ ለማስጀመር እየተሠራ ያለ ሥራ አለ ወይ?
👉 የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?
👉 የኑሮ ውድነት ከፍቷል፤ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚኖሩ ሰዎች መኖር አቅቷቸዋል፤ መንግሥት ይሄን ለመፍታት ምን አስቧል?
👉በአረንጓዴ አሻራ የተጀመሩ ሥራዎች ምን ይመስላሉ፤ ለመጪው ጊዜ የተደረጉ ዝግጅቶች ዙሪያ ማብራሪያ ቢሰጥ?
👉 የኢንዱስትሪውን እና የማንፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማበረታት፣ ማነቆዎችን ለመፍታት እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ላይ ማብራሪ ቢሰጥ?
👉 በ2016/17 የምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያን በወቅቱ ለማስገባት የተደረገው ጥረት ጥሩ ነው፣ ነገር ግን በክልሎች ላይ የሥርጫት ችግር እንዳለ ይነሳል፤ ችግሩን ለመፍታት ምን እየተሠራ ነው?
👉ሀገራችንን ለምስቅልቅል የሚዳርጋት መንግሥታዊ ሌብነት ነው፤ ሙስና የሀገርን መዋቅር የሚበላ፣ የሕዝብን ማኅበራዊ ትስስር የሚበጣጥስ፣ የሕግ የበላይነትን የሚሸረሽር፣ ሀገር እንዳታድግ የሚያደርግ ነው፡፡ ሙስናን ለመከላከል የተቋቋመው ሀገራዊ ምክር ቤት እዚህ ግባ የሚባል ሥራ አልሠራም፤ መንግሥት ሙስናን ለመከላከል በቁርጠኝነት እየሠራ አይደለም። የመንግሥት መዋቅር በሌቦች ተጠልፏል። መንግሥታዊ አገልግሎት ለማግኘት በእጅ መንሻ ኾኗል። በማስረጃ የቀረበውን የሙስና ቅሬታ ለመመለስ መንግሥት ምን ያክል ቁርጠኛ ነው? ሕዝብ በሙስና ጉዳይ ከመንግሥት ምን ይጠበቅ?
👉 በአዲስ አበባ ከተማ የተሠሩ የኮሊደር ልማቶች ሰው ተኮር እና በሳል መሪነት የተሰጣባቸው ናቸው፡፡
👉በልማቱ ዐይነ ሥውራን የመማር እድል እንዲኖራቸው የመማሪያ ቦታ መዘጋጀቱ የሚደነቅ ነው፡፡
👉 በኢትዮጵያ በየጊዜው የእርስ በእርስ ግጭቶች እየተፈጠሩ ነው፤ የሚፈቱበት መንገድ በውይይት እና ድርድር ከመኾን ይልቅ፣ አንደኛውን አሸናፊ ሌላኛውን ተሸናፊ በማድረግ ለትውልድ የሚተርፍ ቁርሾ እያስቀመጠ ነው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገለጸ።
Next articleየሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያነሷቸው ጥያቄዎች፡-