
ባሕር ዳር: ሰኔ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፀጥታና ደኀንነት የጋራ ግብር ኃይል ከሐምሌ 3 እስከ 11 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12 ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።
ተማሪዎች የለፉበትን የትምህርት ውጤት ማግኘት ይችሉ ዘንድ ፈተናው ያለምንም የፀጥታ ችግር በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለፈተና ቁሳቁሶች እጀባ፣ ጥበቃ እና ፍተሻ እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ኅብረተሰቡ ይህንን ዐውቆ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ግብረ ኀይሉ መጠየቁን ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ሲመለከትም የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ባዘጋጀው የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) በመጠቀም ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር በመደወልና መልዕክት በመላክ ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አካላት በአካል ጥቆማ እንዲሰጥ ግብረ ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!