እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ነገ ተማሪዎቹን ያስመርቃል፡፡

22

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም 696 ተማሪዎችን ለማስመረቅ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አዕምሮ ታደሰ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም ተማሪዎቹን በመጀመሪያ ዲግሪ እና በሁለተኛ ዲግሪ እንደሚያስመርቅ ነው ዶክተር አዕምሮ ያስታወቁት፡፡

ለአምስተኛ ዙር በመጀመሪያ ዲግሪ 428 ተማሪዎችን፣ በሁለተኛ ዲግሪ 268 ተማሪዎችን በአጠቃላይ 696 ተማሪዎቹን ለማስመረቅ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቋል ነው ያሉት፡፡ ከዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች መካካል 183 ሴቶች መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ ለአምስት ዓመት ከአስተማራቸው 41 የሕግ ተማሪዎች ውስጥ 32ቱ የመውጫ ፈተናውን አልፈው የሚመረቁ እንደኾኑም ለአሚኮ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ሰሎሞን ስንታየሁ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ክትባት ያልጀመሩ እና ጀምረው ያቋረጡ ሕጻናትን ቤት ለቤት በመሄድ አገልግሎት እየተሰጠ ነው” ጤና ቢሮ
Next article“ለዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ እና ለመደበኛ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዝግጅት ተደርጓል” የጭልጋ ወረዳ