
ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት ክብር” በሚል መሪ መልእክት ከዞን እና ከወረዳ መሪዎች ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በዞኑ መልማት የሚችል ሰፊ መሬት እና ማልማት የሚችል የሰው ኃይል ቢኖርም በዞኑ በአንዳንድ ወረዳዎች እርዳታ የሚፈልግ ኅብረተሰብ ይገኛል ብለዋል የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ ወርቁ ኀይለማርያም።
በመኾኑም ያለንን ሀብት ተጠቅመን ከኅብረተሰቡ ጋር በቅንጅት በመሥራት በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ይገባናል ነው ያሉት።
ዋና አሥተዳዳሪው አያይዘው ባለፉት ዓመታት በተከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች የተገኘውን ውጤት በዘንድሮው ዓመትም አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።
በዞኑ እየመጣ የሚገኘውን ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠልም በኅብረተሰቡ ዘንድ የሚነሱ ጥያቄዎችን
ለመመለስ በትኩረት እንሠራለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!