
አዲስ አበባ: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የያዘችውን ዕድገት ለማፋጠን ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ.ር) ገልጸዋል፡፡ በሀገሪቱ ቀልጣፋ፣ ምቹ እና ዘመናዊ የትራንስፖርት ሥርዓት እንዲኖር ለማድረግ ሥራዎች በስፋት መሠራታቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ከአውቶ ቴክ ትሬዲንግ ጋር በመተባበር በትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ በአውቶሞቲቨ ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ አውቶሞቲቭ ትራንስፖርት ኤክስፖም በሚሊኒየም አዳራሽ ተከፍቷል። ኤክስፖው ከሰኔ 26/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተገለጸው።
በዚህ አውቶሞቲቨ ትራንስፖርት ኤክስፖ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ዘርፍ የተሰማሩ ባለ ሃብቶች፣ የካምፓኒ ተወካዮች እና የሥራ ፈጣሪ ወጣቶች ታዳሚ ኾነዋል።
ዘጋቢ፡- ሰለሞን አሰፌ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!