
ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በጅቡቲ የዶራሌ ሁለገብ ወደብ ተገኝተው የኢትዮጵያ አጠቃላይ የገቢ-ወጪ የዝውውር ሂደቱን ተመልክተዋል። በመስክ ምልከታቸውም የዘንድሮ የአፈር ማዳበሪያ ኦፕሬሽን ሂደትን ተዘዋውረው ጎበኝተዋል።
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ማኀበራዊ ትስስር ገጽ እንዳሰፈረው ሚኒስትሩ በታጁራ ወደብ ተገኝተው ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገውን የድንጋይ ከሰል ዝውውር ሂደትም ተመልክተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!