ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋር ተወያዩ።

15

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ጠዋት የማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዝዳንት እና ዋና ሥራ አሥፈጻሚ አንቶኒ ካፑአኖ ጋር ተገናኝተው በማደግ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ የጉዞ እና የሆስፒታሊቲ ዘርፍ ላይ ተወያይተዋል።

በባሕል ሃብቷ እና ታሪካዊ ቅርስ ይዞታዋ ብሎም በአስደናቂ የመልክዓ ምድር ገጽታዋ የታወቀችው ኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንደስትሪዋን በማስፋፋት ላይ አተኩራለች።

በዓለም ዙሪያ 8785 ያህል ቅርንጫፎች እና የሃብት አድራሻዎች በመያዝ በመስተንግዶ እና ማረፊያ አገልግሎት ዘርፍ መሪ የሆነው ማሪዮት ኢንተርናሽናል በዚህ ሥራ ጉልህ ሚና ለመጫወት እየሠራ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ፕሬስ ዘግቧል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ እንደሚሠራ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
Next article“የተፈተነው ትራንስፖርት እና የበዛው የሕዝብ እንግልት”