የሆቴሎች የኮኮብ ደረጃ ምደባ በአዲስ መልክ እንደሚሠራ የቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

15

ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ከመስከረም ጀምሮ ከዚህ በፊት የተሰጠው የኮኮብ ደረጃ ሥራ ላይ እንደማይውል የቱሪዝም ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደረጃ ምደባ ደንብ ሆቴሎች በየሦስት ዓመቱ በዳግም የደረጃ ምደባ ሂደት ማለፍ እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡

በዚህም መሠረት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአዲስ አበባ ከተማ እና በክልሎች የሚገኙ ሆቴሎችን የደረጃ ምዘና ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡ ይህንን ለማድረግ የሚያስችለው መመሪያ ላይም ከሆቴል ባለቤቶች እና ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የቱሪዝም ሚንስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ አሁን በሚደረገው የዳግም የደረጃ ምዘና ሂደት ውስጥ የማያልፉ ሆቴሎች ከዚህ ቀደም የተሰጣቸው የኮኮብ ደረጃ በሕጉ መሠረት የአገልግሎት ጊዜው ያበቃ በመኾኑ የኮኮብ ደረጃው እንደሚሰረዝ ተናግረዋል፡፡ ይህ የዳግም ምደባ በዋናነት ሆቴሎች የሚሰጡትን አገልግሎት ማሻሻል እና የሀገሪቱን የቱሪዝም አገልግሎት ተወዳዳሪነት ማሳደግ ላይ ትኩረቱን ያደረገ መኾኑንም ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየክልሉን ሰላም ወደነበረበት ለመመለስ ወጣቶች ከሰላም ካውንስሉ ጎን ሊቆሙ እንደሚገባ የሰቆጣ ከተማ ወጣቶች ተናገሩ።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከማርዮት ኢንተርናሽናል ፕሬዚዳንት እና ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋር ተወያዩ።