
ባሕር ዳር: ሰኔ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ የአረንጓዴ አሻራ ዋናው የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋሚያና የአረንጓዴ ልማት ማሳኪያ ተጨባጭ ዕርምጃችን ነው ብለዋል። ዛሬ የወቅቱ የዓለማችን ወሳኝ አጀንዳ በሆነው የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ዕቅድ ማስተግበሪያ መርሐ ግብር ላይ ታድመናል ነው ያሉት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት፡፡
ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆነው የስንዴ ልማት ፕሮግራማችን በአየር ንብረት ለውጥ እየደረሰብን ያለውን ተጽዕኖ እንድንቋቋምና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ ምላሽ ለመስጠት አቅም ሆኖናል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል የታዳሽ ኢነርጂ አቅርቦት ሥራ ሀገራችንን ከኢ-ታዳሽ የኢነርጂ ምንጭ ወደ ታዳሽ ምንጭ የቀየረ ነው ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ።
በመሆኑም ሀገራችን የቀረጸቻቸውን የአየር ንብረት እና የአካባቢ ፖሊሲዎችና ዕቅዶች በአግባቡ እንዲፈጸሙ መላው የሀገራችን ሕዝብ እና አጋር አካላት በአንድነት መንፈስ እንድትሳተፉ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!