
ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ ከጀርመን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሄኮ ኒትዝሺከ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። አምባሳደር ምስጋኑ በውይይታቸው ወቅት ጀርመን የኢትዮጵያ ቁልፍ ስትራቴጂክ አጋር መኾኗን ገልጸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ስላለው ጠንካራ ግንኙነት አብራርተዋል።
የጀርመን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሄኮ ኒትዝሺከ በበኩላቸው ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ቁርጠኛ መኾኗን ገልጸዋል። ሁለቱ ወገኖች የጋራ ፍላጎቶችን መሠረት ባደረገ መልኩ በወቅታዊ የአፍሪካ ቀንድ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው በውይይቱ ላይ ኢትዮጵያ በቀጣናው ወሳኝ ሚና ያላት ሀገር መኾኗን ልዩ መልዕክተኛው ተናግረዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!