ከ1 ሚሊዮን በላይ ሕጻናትን ለመከተብ የ10 ቀናት ዘመቻ ይፋ ተደረገ።

16

ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጤና ሚኒስቴር ከዛሬ ጀምሮ ለ10 ቀናት የሚቆይ የክትባት ዘመቻ ይፋ አድርጓል፡፡

የክትባት ዘመቻው ክትባት ላልጀመሩ እና ጀምረው ላቋረጡ ከ5 ዓመት በታች ለኾኑ ሕጻናት እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ በዘመቻው ከ1 ሚሊዮን በላይ ሕጻናት ተጠቃሚ ይኾናሉ። ለክትባቱ አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውም ተጠቁሟል።

ዘመቻው የሚካሄድባቸው ከ1 ሺህ በላይ ወረዳዎች የተለዩ ሲኾን ለተፈናቃዮች፣ ወረርሽኝ ላለባቸው አካባቢዎች እና ራቅ ላሉ ወረዳዎች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ከጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመንግሥት ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።
Next articleየፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል በሚል የቀረቡለትን 12 ጉዳዮች መርምሮ አጸደቀ።