
ባሕር ዳር: ሰኔ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ሸዋ ዞን እንሳሮ ወረዳ ለሚ ናሽናል ሲሜንት ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመንግሥት ሠራተኞች የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
የችግኝ ተከላው የተካሄደው በብዟየሁ ታደለ ፋውንዴሽን እና በወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች የጋራ ትብብር እንደኾነ ተገልጿል። በችግኝ ተከላው የወረዳ መሪዎች እንዲሁም የፋብሪካው ሠራተኞች እና መሪዎችም ተገኝተዋል።
ከችግኝ ተከላ ሥነ ሥርዓት በኋላም መንግሥት ሠራተኞቹ ፋብሪካውን መጎብኘታቸውን ከሰሜን ሽዋ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!