የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር ይወያያል።

37

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን በ35ኛ መደበኛ ስብሰባው ነገ በልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ ቀዳሚ ባደረገው አጀንዳው የፌዴራል መንግሥት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ በዝርዝር እንደሚወያይ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

በመቀጠል በኩዌት እና በኢትዮጵያ መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የሚቀርበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ የሚያፀድቅ ነው የሚሆነው።

በተጨማሪም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እንደገና ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን እንዲሁም የኢሚግሬሽን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል።

በመጨረሻም የፌደራል መንግስት ሠራተኞች ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀርበበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ረቂቅ አዋጁን ያፀድቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ወጣቶች በሀገር ግንባታ ላይ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እድል ይፈጥራል” አቶ ብናልፍ አንዱዓለም
Next articleየማንነትና የአስተዳደር ወሰን ጥያቄዎችን ሕግንና የዜጎችን ዘላቂ አብሮነት መሰረት ባደረገ መልኩ ምላሽ ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ገለጸ።