
ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኅላፊዎች በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ የሚገኘውን የአኮቦ ኢትኖ የማዕድን ኩባንያን ጎበኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳደር ኡሞድ ኡጁሉ፣ የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ.ር)፣ ሚኒስትር ድኤታዎች እና የክልሉ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅትም የአኙዋሃ ዞን የሥራ ኅላፊዎች ስለኩባንያው አጠቃላይ ሂደት ገለጻ ያደረጉ ሲኾን ኩባንያው በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር ተናግረዋል፡፡
ኤፍ ቢ ሲ የክልሉን ኮሙኒኬሽን ጠቅሶ እንደዘገበው ከጉብኝቱ በኋላም የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተከናውኗል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!