
ባሕር ዳር: ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በተቋሙ ለበለፀጉ አራት የፈጠራ ውጤቶች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን የፓተንት መብት ማግኘቱን አስታውቋል።
ለኢንስቲትዩቱ የተሰጠው የፓተንት መብት ሰው ሠራሸ አስተውሎት ቴክኖሎጂን መሠረት ያደረጉ የስኳር በሽታ አይነት የሚለይ፣ የጡት ካንስር አይነት የሚለይ፣ የሕጻናት የቆዳ በሽታ ልየታ የሚሠራ ሥርዓት እና የቡና ቅጠል በሽታ ልየታ የሚያደርግ የፈጠራ ውጤቶች እንደኾኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና(ዶ.ር ) ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል የፓተንት መብት የዕውቅና ሰርተፍኬት መቀበላቸውን ከኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!