የፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀረቡትን አጀንዳዎች መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ፡፡

19

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 3ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በምክር ቤቱ የሥብሠባ አዳራሽ ለማካሄድ ለጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎች በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ቀርበዋል፡፡
ጉባኤውም የቀረቡትን አጀንዳዎች መርምሮ በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ምክር ቤቱ በመደበኛ ጉባኤው ላይ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የአፈፃፀም ሪፖርትን ጨምሮ ለጉባኤው የተያዙ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከፊዴሬሽን ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሁለተኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው እየገቡ ነው፡፡
Next articleበማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሰላም ጥሪን ለተቀበሉ ኀይሎች የተሀድሶ ሥልጠና ተሰጠ፡፡