በደሴ ከተማ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች እየተመረቁ ነው።

61

ደሴ: ሰኔ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በደሴ ከተማ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው የተለያዩ የመሠረተ ልማት ሥራዎች የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተመረቁ ነው።

3 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የኮሾም በር ገራዶ አስፋልት መንገድ፣ ከ71 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የቀድሞው ደሴ መናኸሪያ፣ በአማራ ልማት ማኅበር እና በሕዝብ ተሳትፎ የተገነቡ የከነማ ሕዝብ መድኃኒት ቤቶች በዕለቱ ከሚመረቁ ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።

በከተማዋ ግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የተደረገባቸው ሌሎች ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ሲኾኑ በቅርቡ ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉም ተብሏል።

ዘጋቢ፦ አሊ ይመር

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሂዱ እና ወራሪዎችን ድል ንሷቸው፤ በኮሪያ ልሳነ ምድርም ሕግና ሥርዓትን አስከብሩ” አጼ ኃይለሥላሤ
Next articleየዘመናት የሕዝብ ጥያቄ የነበረው የደሴ መናኸሪያ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።