“በርካታ ኀይልን ፈጻሚ ማድረግ የመሪነት ሚና ቢኾንም ውጤታማ መኾን የሚቻለው በትብብር ነው” ከንቲባ አዳነች አቤቤ

40

አዲስ አበባ: ሰኔ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የሕዝብ ተመራጭ ሴቶች ሚና በሀገረ መንግሥት ግንባታ” በሚል መሪ መልእክት ከተማ አቀፍ የማጠቃለያ ንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በርካታ ኀይልን ፈጻሚ ማድረግ የመሪነት ሚና ቢኾንም ውጤታማ መኾን የሚቻለው በትብብር መኾኑን ከንቲባ አዳነች አቢቤ ተናግረዋል።

ከተማን ከማስዋብና ማልማት ባለፈ ሰው ላይ መሥራት እንደሚያስፈልግም ነው ከንቲባዋ የተናገሩት፡፡ ሰዎች ሕዝባቸውን ለማገልገል ራሳቸውን ከሠጡ ሁለንተናዊ ዘላቂ ልማትን ማምጣት ይቻላል ብለዋል፡፡

በብዙ ጫና ውስጥም ኾነው ሀገራቸውን በትጋት የሚያገለግሉ ሴቶችን ማበረታታት እንደሚያስፈልግም ከንቲባ አዳነች ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልቃድር በሰላምና ልማት እንዲሁም የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ሴት መሪዎች በትኩረት ሊሠሩ ይገባል ብለዋል፡፡

አፈጉባኤዋ የሴትነት ጥበብን ለሀገረ መንግሥት ግንባታ ማዋል እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።

የምክር ቤቱ አባላት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ላመጡት ሁለንተናዊ ለውጥ ዕውቅናና ሽልማት ሰጥተዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ዩኒቨርሲቲው ለጎረቤት ሀገራት የፖሊስ ሠራዊትና መኮንኖች የሚሰጠው የትምህርት ዕድል የሚያኮራ ነው” ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ
Next article“ሂዱ እና ወራሪዎችን ድል ንሷቸው፤ በኮሪያ ልሳነ ምድርም ሕግና ሥርዓትን አስከብሩ” አጼ ኃይለሥላሤ