
ባሕር ዳር: ሰኔ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ዛሬ ከደሴ ከተማ ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር መገናኘታቸውን ገልጸዋል።
በቆይታችን በሁሉም ቦታ እጅግ አመርቂ የኾኑ ሥራዎች እየተሠሩ መኾናቸውንም አረጋግጠናል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት
ተባብረን ከሠራን የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እንደምናስረክብ ምንም ጥርጥር የለውም ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!