
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ በሥርዓተ ምግብ ላይ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ በሀራ ከተማ አካሂዷል፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ የኒውትሬሽን ኦፊሰር ጌትነት ዋለ እንደገለጹት ጤናማ እና አምራች ማኅበረሰብ ለመገንባት በሚደረገው ሁለንተናዊ ርብርብ በሥርዓተ ምግብ ላይ አበክሮ መሥራት ይገባል፡፡
የዞን የኒውትሬሽን ፎካል ፐርሰኖች እና የሶቆጣ ቃል ኪዳን አስተባባሪዎች ሥርዓተ ምግብን እንደ ዋና ተግባራቸው አድርገው እንዲሠሩም አሳስበዋል፡፡
በሰሜን ወሎ ዞን ጤና መምሪያ በዩኒሴፍ የዞን የሥርዓተ ምግብ አስተባባሪ ታደገ ዓለማየሁ እንደተናገሩት ሕጻናት ከዕድሜአቸው እና ከክብደታቸው አንፃር የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ በማድረግ የሕጻናትን ህመም እና ሞት መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡
አቶ ዓለማየሁ የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ በሥርዓተ ምግብ ጉድለት ምክንያት በሕጻናት ላይ የሚከሰቱ የጤና ችግሮችን ቀድሞ ለመከላከል የዞን የኒውትሬሽን ፎካል ፐርሰኖች እና የሰቆጣ ቃል ኪዳን አስተባባሪዎች የላቀ ድርሻ ያላቸው በመኾኑ እስከ ወረዳ ድረስ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ ለውጤታማነቱ መትጋት አለባቸው ማለታቸውን ከሰሜን ወሎ ዞን ኮሙዩኒኬሽ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!