
ደሴ: ሰኔ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ በ2016 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ለነበራቸው አባላት ዕውቅና እና ሽልማት አበርክቷል።
የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ጌታቸው ሙህየ በበጀት ዓመቱ ሰላምን በማረጋገጥ፣ ፈጣን አገልግሎት በመስጠት እና ግዳጅን በመወጣት ጥሩ አፈጻጸም ለነበራቸው የፖሊስ አባላት ዕውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል ብለዋል።
ተሸላሚዎች ወደፊትም የከተማዋን ሰላም በማስከበር፣ ለማኅበረሰቡ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።
ተሸላሚ የፖሊስ አባላት ምክትል ኢንስፔክተር አሕመድ ሙሄ እና ዋና ሳጅን ከድር የሱፍ ለተሰጣቸው ዕውቅና እና ሽልማት አመሥግነው ዕውቅናው ቀጣይ ሥራዎችን በተሻለ ለመፈፀም እንደሚያበረታ ነው የተናገሩት።
በዕለቱ የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመከላከያ ሠራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡- ከድር አሊ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!