
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሩሲያ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የብሪክስ አባል ሀገራት የጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚዳንቶች የተሳተፉበት ፎረም ተጠናቋል፡፡
ፎረሙ ከሰኔ 10/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ14/2016 ዓ.ም “ብሪክስ ቺፍ ጀስቲስ ፎረም” በሚል ርዕሰ ጉዳይ ነው ምክክሩ የተካሄደው፡፡
በመድረኩም በፍርድ ቤቶች አሠራር፣ በዜጎች የማኅበራዊ መብቶች አጠባበቅ፣ በኢንቨስተሮች መብት ጥበቃ፣ በመሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች እና ነፃነቶች ጥበቃ ላይ ነው ምክክር የተደረገው፡፡
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት፣ የፍርድ ቤቶችን አሠራር የሚያዘምን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የብሪክስ አባል ሀገራት ሕግጋት ላይ የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ዙሪያም ውይይት መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ቴዎድሮስ ምኅረት በአቅም ግንባታ ረገድ ከሩሲያ በተጨማሪ ከሕንድ፣ ከቻይና እና ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች አቻዎቻቸው ጋር በትብብር በሚሠሩበት ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!