የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡

58

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ከሰኔ 13/2016 ዓ.ም እስከ ሰኔ 14/2016 ዓ.ም ድረስ ሲሰጥ የቆየው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ገልጿል፡፡ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

ፈተናውን ከማጓጓዝ ጀምሮ ተማሪዎች ተፈትነው እስከሚያጠናቅቁ ድረስ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ የትምህርት መሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እና ተማሪዎች መሳተፋቸውን ነው ያብራሩት፡፡ ለዚህ ሥራቸው ደግሞ ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው በቀጣይ ከሐምሌ 3/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለምንም እንቅፋት እንዲጠናቀቅ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ሁሉ የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ዶክተር ሙሉነሽ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከ1ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ተሠራጭቷል” የምሥራቅ ጎጃም ዞን
Next article“በዞኑ 82 የንፁህ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ ነው” የሰሜን ወሎ ዞን