
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ኀላፊ አበበ መኮነን እንደገለጹት ለምርት ዘመኑ አገልግሎት የሚውል1ሚሊዮን 544ሺህ 956 ኩንታል ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ግዥ ተፈጽሟል፡፡ ኀላፊው ግዥ ከተፈጸመው ውስጥ 1ሚሊዮን 263 ኩንታል ማዳበሪያ ወደ ወረዳ በማድረስ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ገልጸዋል።
አቶ አበበ ወደ ወረዳ ከገባው ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ ውስጥ 90 ነጥብ 5 በመቶ ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን ነው ያስገነዘቡት፡፡ ለምርት ዘመኑ ከቀረበው 14ሺህ 309 ኩንታል የበቆሎ ምርጥ ዘር ውስጥ 13ሺህ 868 ኩንታል ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱንም ገልጸዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንዳለው የግብርና መምሪያው ለ2016/17 የምርት ዘመን 612ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል በመሸፈን 23 ሚሊዮን 300ሺህ ኩንታል ምርት ለማግኘት አቅዶ እየሠራ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!