
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ጸሐፊ ክላቨር ጋቴትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡ ሁለቱ ኅላፊዎች ኢትዮጵያ በመጭው ሀምሌ ወር የምታስተናግደው 4ኛዉ ፋይናንስ ለልማት ጉባዔ የቅድመ ዝግጅት ስብሰባ የተሳካ እንዲኾን ለማድረግ በጋራ መሥራት ባለባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አድርገዋል፡፡
በቀጣይ መስከረም ወር በኒውዮርክ በሚካሄደው የመንግሥታቱ ድርጅት ስብሰባ ላይ ሊኖር በሚገባቸው ተሳትፎዎች ዙሪያም የሀሳብ ልውውጥ አድርገዋል። በተጨማሪም ሁለቱ ኅላፊዎች ኮሚሽኑ እና ኢትዮጵያ በልማት እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ተባብረው መሥራት በሚችሉበት አግባብ ላይ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!