
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)
በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥዳደር ሲሰጥ የነበረው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኅላፊ ሰይፈ ሞገስ ገልጸዋል። በ179 ትምህርት ቤቶች 5ሽህ 926 ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ የገለጹት ኅላፊው በቀጣይም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናውን በሰላም ለማስፈተን መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
በአካባቢያቸው ያለው አንጻራዊ ሰላም ፈተናውን በተረጋጋ መንገድ አንዲፈተኑ ከማድረጉም በሻገር የጸጥታ መዋቅሩ በተጠናከረ መንገድ እንዲንቀሳቀስ አግዞናል ያሉት ደግሞ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኅላፊ ሃምሣ አለቃ አዘዘው አዳነ ናቸው።
የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናን በሰላም ለማጠናቀቅ የተሠራው ተግባር ለ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በሰላም መጠናቀቅ አግዞናል ያሉት ሃምሳ አለቃ አዘዘው አዳነ በቀጣይም የብሔረሰብ አስተዳደሩን ሰላም ለማስጠበቅ እንሠራለን ብለዋል።
ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!