“በተገኘው አንጻራዊ ሰላም የተሟላ የፍትሕ አገልግሎት ለመስጠት እየሠራሁ ነው” የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር

19

ደብረ ማርቆስ: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፍትሕን እና መልካም አሥተዳደርን በዘላቂነት ማረጋገጥ የሚቻው ሰላም ሲረጋገጥ ነው፡፡ በክልሉ ባጋጠመው የጸጥታ ችግር ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ ኾኖ ቆይቷል፡፡ በተለይ ዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብታቸው ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ንጉሴ ብናልፈው አሁን በተገኘው አንፃራዊ ሰላም በከተማ አሥተዳደሩ የተሟላ የፍትሕ አገልግሎት ለመስጠት እና አጠናክሮ ለማሰቀጠል እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ በቀውሱ ምክንያት የሴቶች እና የሕጻናት ሃብት እና ንብረት ያላግባብ ተነጥቀው እንደነበር ኀላፊው ጠቅሰዋል፡፡ ፍትሕ አጣን ላሉት የኅብረተሰብ ክፍሎችም ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በተገኘው አንፃራዊ ሰላም በሰነዶች እና ጠበቆች አገልግሎት ከውል እና ማስረጃ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ኅብረተሰቡ የተጠናከረ አገልገሎት እያገኘ ስለመኾኑም ኀላፊው ተናግረዋል፡፡ ተገቢውን ፍትሕ መስጠት እንዲቻል እና ለዜጎች የሰላም ዋስትና ለመፍጠር የሃይማኖት አባቶች ኅብረተሰቡ እና መንግሥት ለሰላም መረጋገጥ ኀላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳሰበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article” ከችግር ለመውጣት ተስማምተን እና አንድ ኾነን መሥራት መቻል አለብን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleየመንግሥት ሠራተኞች የደረጃ እድገት እና የእርከን ጭማሪ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ተፈቅዷል ተባለ።