በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ለተገነባው የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት መዋቅራዊ አደረጃጀት እየተዘጋጀ መኾኑ ተገለጸ፡፡

28

ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ተገንብቶ በቅርቡ የተመረቀው ሼይካ ፋጢማ የዐይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት መተዳደሪያ ደንብ፣ ስትራቴጂክ ዕቅድ እና መዋቅራዊ አደረጃጀት እየተዘጋጀ መኾኑን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር ፀጋዬ አሰፋ አዳሪ የትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ መዋቅራዊ አደረጃጀት እና ስትራቴጂክ ዕቅድ በትምህርት ባለሙያዎች እና መምህራን እየተዘጋጀ መኾኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ.ር) ከቢሮው አማካሪ ጥላሁን ፍቃዱ ጋር በመኾን ሼይካ ፋጢማ የዓይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ተገኝተው ባለሙያዎቹ እያዘጋጁ የሚገኘውን መተዳደሪያ ደንብ፣ ስትራቴጂክ ዕቅድ እና መዋቅራዊ አደረጃጀት ሂደትን ተመልክተዋል፡፡

ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ጠቅሶ ኢቢሲ እንደዘገበው ቢሮ ኀላፊው ምልከታ በማድረግ የሥራ አቅጣጫ መስጠታቸው ታውቋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአዕምሮ ጤና እና ሌሎች የአካል ክፍሎቻችን ያላቸው ግንኙነት ምንድን ነው?
Next article“በማዕድን ዘርፍ ላይ እሴት ያልተጨመረበት የማዕድን ሃብት ወደ ውጪ እንዳይወጣ የሚል ሕግ እየተረቀቀ ነው” ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኝ