
ደብረ ማርቆስ: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የንግድ እና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አስቻለ አላምሬ ከምሥራቅ ጎጃም ዞን እና ከደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ነዋሪዎች ጋር ሰላምን ለማምጣት ያለመ ውይይት ሲያያደርጉ ቆይተዋል። ከሕዝቡ ጋር በነበሯቸው የውይይት መደረኮች ሕዝቡ በክልሉ የተከሰተው የሰላም እጦት በንግግር እና በይቅርታ እንዲፈታ እንደሚፈልግ ተገንዝቤያለሁ ብለዋል።
“ኢትዮጵያዊን አጀንዳዎቻቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቅረብ በውይይት እንዲፈቱ ማድረግ አለባቸው” ያሉት አቶ አስቻለ በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት የሕዝቡን ጥየቄዎች እና አጀንዳዎች ለመሰብሰብ እንዲሁም ወኪሎችን ለመምረጥ ጫና ማሳደሩን ገልጸዋል። በንግግር መፍታት የምንችላቸውን ችግሮች በነፍጥ ለመፍታት በማሰብ በሚካሄድ ግጭት ምክንያት የሚፈሰው የሰው ልጆች ደም ሊቆም እንደሚገባም አሳስበዋል።
ክልሉ በግጭቱ ምክንያት ከደረሰበት ውድመት እንዲያገግም እና ለመልሶ ግንባታ ከፌደራል መንግሥቱ ጀምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አስገንዝበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!