የመከላከያ ጀኔራል መኮንኖች አዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር ተወያዩ።

225

ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ መከላከያ ጀኔራል መኮንኖች አዲስ አበባ ከሚኖሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር በዓድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአማራ ክልል የሰላም ኮንፈረንሰ ውይይት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተደርጓል፡፡ ወይይቱን የመሩት የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰ፣ የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል ኮሚሽነር ዘላለም መንግሥቴ እንዲሁም የመከላከያ ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል በላይ ስዩም ናቸው።

ተሳታፊዎችም አሉ የሚሏቸውን ችግሮች ያነሱ ሲሆን ጥያቄዎቻቸው ለክልሉ መንግሥት እና ለፌደራል መንግሥት ተደራጅቶ እንደሚቀርብ ተመላክቷል። በውይይቱ ማጠቃለያ የመድረኩ ተሳታፊዎች ባለ 7 ነጥብ የአቋም መግለጫ ማውጣታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአገልግሎት አሰጣጣችንን ዘመናዊ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ቴክኖሎጂን የሪፎርሙ መሠረት ማድረግ ይገባናል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ
Next article“ኢትዮጵያዊን አጀንዳዎቻቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በማቅረብ በውይይት እንዲፈቱ ማድረግ አለባቸው” አስቻለ አላምሬ