በጎንደር ቀጣና የሁሉም ዞኖች ተወካይ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የሰላም ኮንፈረንስ ተካሄደ።

10

ጎንደር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ቀጣና ከሰኔ 11 እስከ 12/2016 ዓ.ም የተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ ባለሰባት አቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

በዚኽም መሠረት:
1. በፖለቲካ፣ በመልካም አሥተዳደር፣ በማኀበራዊ እና በሰላም ጉዳይ የተነሱ ጥያቄዎች በየፈርጃቸው ለከተማ፣ ዞን፣ ክልል እና ለፌደራል መንግሥት እንዲቀርቡ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

2. በክልሉ እና በቀጣናው ያሉ የልማት ጥያቄዎች ያለሰላም ሊታሰቡ ስለማይችሉ ቅድሚያ በክልሉ ውስጥ ማንኛውንም ጥያቄ በሰላም እንዲፈታ ተሳታፊዎች የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት የጋራ አቋም ይዘዋል።

3. ለሚዲያ ተቋማት እና ሙያተኞች እንዲሁም ለማኀበረሰብ አንቂዎች በተላለፈ መልእክት የክልሉ ሕዝብ የቆየበትን ሁለንተናዊ ችግር ተገንዝበው ሕዝብን ወደ ሰላም የሚመልስ እና የክልሉ ሕዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በጋራ የገነባትን ሀገር ተከባብሮ እና ተዘዋውሮ እንዲሠራባት የሚዲያውን አየር በሰላም እንዲሞሉት በታላቅ እክብሮት ጠይቀዋል፡፡

4. ለመንግሥት ባለስልጣናት፣ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ምሁራን፣ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን በአጠቃላይ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ባስተላለፉት መልእክት ለክልሉ ሰላም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

5. ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን በሚል ታጥቀው ጫካው ውስጥ ለሚገኙ ወንድሞች ደግሞ ጥያቄያቸውን በሰላም እንዲያቀርቡ ወገናዊ ጥሪ አቀርበዋል።

6. በመጨረሻ የፌደራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ክልሉ ሰላም እንዲኾን የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የሕጻናት ማቆያ ሠርቶ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ።
Next article“ለመሠረታዊ ማኅበራት ከደረሰው የአፈር ማዳበሪያ 90 በመቶ የሚኾነው ወደ አርሶ አደሩ ተሰራጭቷል” የአማራ ክልል ኅብረት ሥራ ማኅበራት ማስፋፊያ ባለሥልጣን