
ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።
በምልከታው የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ የልማት ሥራዎችን የአፈጻጸም ደረጃ እየተመለከቱ ነው። ከምልከታ በኋላ የቀጣይ አቅጣጫ እና መመሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!