“በሀይል የሚፈታ ችግር ባለመኖሩ እርቅ እና ይቅርባይነትን ልናስቀድም ይገባል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር.)

36

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር.) በክልሉ ለወራት የቀጠለው የሰላም እጦት ለታሪካችን የማይመጥን እና ሕዝቡን ለከፋ ችግር የጣለ መኾኑን ተናግረዋል። ሁሉም ሰው ችግሩን እና ያስከተለውን ጫና ቆም ብሎ በማሰብ ሰላም እንዲፈጠር ኅላፊነቱን መወጣት አለበት ብለዋል።

መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ በቅንነት በመመልከት ወደ ግጭት የገቡ ወገኖች ወደ ሰላም መመለስን ቀዳሚ መፍትሄ አድርገው ሊወስዱት እንደሚገባም አስገንዝበዋል። በሃይል የሚፈታ ችግር እና የሚመጣ አንድነት ባለመኖሩ ችግሮችን በሠለጠነ መንገድ በንግግር በመፍታት እንዲሁም እርቅ እና ይቅርባይነትን በማስቀደም በግጭት ምክንያት ችግር ውስጥ የገባውን ሕዝብ ልንታደግ ይገባልም ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ኢትዮጵያ በብሪክስ አባል ሀገራት መካከል በተካሄዱት ሥብሠባዎች ስኬታማ ውይይቶችን አድርጋለች” አምባሳደር ነብዩ ተድላ
Next article1 ሺህ 061 የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልል አቀፍ ፈተና እየወሰዱ መኾኑ የወልድያ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።