ከ5 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል ፈተና እየወሰዱ መኾኑን በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስታወቀ።

16

ሁመራ: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠው የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና በአማራ ክልል በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን መሰጠት ተጀምሯል። በ132 ትምህርት ቤቶች 5 ሺህ 110 ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ገብረ ማርያም መንግሥቴ ገልጸዋል።

በአካባቢው አንጻራዊ ሰላም በመኖሩ ተማሪዎች ዓመቱን ሙሉ ትምህርታቸውን ያለማቆራረጥ ሲከታተሉ እንደነበር ነግረውናል። ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር በዞኑ እየተሰጠ እንደሚገኝ አንስተው ተማሪዎች በፈተናው ውጤታማ እንዲኾኑ የተለያዩ ድጋፎች ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

የአካባቢው ሰላም መኾን በክልል ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተሰጠ የሚገኘውን የ6ኛ ክፍል ፈተና ተማሪዎች የተሻለ ዝግጅት በማድረግ ውጤታማ እንዲኾኑ ያስችላል ብለዋል። አሚኮ ምልከታ ባደረገበት በቃብትያ ሁመራ ወረዳ በአደባይ፣ በእድሪስ፣ በዘርባቢ እና ፈረስ መግሪያ ቀበሌዎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላም እየተሰጠ ይገኛል።

ዘጋቢ :- ያየህ ፈንቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት መሠረታዊ ወታደሮችን እያስመረቀ ነው።
Next articleየምሥራቅ ጎጃም ዞን ሕዝብ ያጣውን ሰላም እንዲያገኝ በቁርጠኝነት እየሠሩ መኾናቸውን የዞኑ መሪዎች ገለጹ።