
ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመከላከያ የሰላም ማስከበር ማዕከል ሁርሶ የኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ወታደርነት ያሠለጠናቸውን ወታደሮች እያስመረቀ ነው። ማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ ዛሬ በመሠረታዊ ወታደርነት እያስመረቃቸው የሚገኙት ወታደሮች የ8ኛ ዙር ሠልጣኞች ናቸው።
እየተመረቁ የሚገኙት አዳዲስ መሠረታዊ ወታደሮች በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው የቀሰሙትን የንድፍ እና የተግባር ወታደራዊ ሥልጠና በተግባር እያሳዩ ይገኛሉ። በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የዕለቱ የክብር እንግዳ በኢፌድሪ የመከላከያ ሚኒስቴር በመከላከያ ሕብረት የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አጫሉ ሸለመና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንንኖች እና ሌሎች የኅብረተሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ እና በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቲንጀንት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ለተመራቂዎቹ የሥራ መመሪያ ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!