
ደብረ ብርሀን: ሰኔ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) መምሪያው የ2016 ዓ.ም የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ መልእክት የመክፈቻ መርሐ ግብር አካሂዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሀን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በበጎ ፈቀድ አገልግሎቱ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ታሳቢ ያደረጉ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል፡፡
የደም ልገሳ፣ የከተማ ጽዳት እና ውበት፣ የአቅም ደካሞች ቤት ጥገና፣ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች ማኀበራዊ ሥራዎች በበጎ ፈቃደኞች ከሚከናወኑት ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ናቸው ተብሏል፡፡ የደብረ ብርሀን ከተማ ወጣቶች እና ስፓርት መምሪያ ኅላፊ አቶ አውራሪስ አረጋ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ላይ የሚሳተፉ ወጣቶች ባላቸው አቅም እና ጸጋ ልክ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል ።
በዚህ ሥራ ውስጥ 59ሺ 874 ወጣቶችን ተሳታፊ በማድረግ 154 ሺህ ወገኖችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ኅላፊው ተናግረዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳትፎው ወደ ገንዘብ ሲቀየር ከ70 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት እንደሚኾን አቶ አውራሪስ ተናግረዋል፡፡ ፡
ስንታየሁ ሀይሉ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!